Song Lyrics

ፍቅሩን ቀምሼአለሁ

Daniel Amdemichael
Mogninet Hono Ayidelem
አዝ፦ ፍቅሩን ቀምሻለሁ ምሕረቱን አይቼዋለሁ ድንቅ ነው በሕይወቴ ያረገዉ መድኃኒቴ ኦ ኃያል ሥሙን ኢየሱሴን ልባርከው (2x) ምሕረቱን አይቻለሁ (2x) ላመልከው ፈቅጃለሁ ድንቅ ነው በሕይወቴ (2x) ያረገው መድኃኒቴ ጉልበቴን አስገዛሁለት አምላኬን ሁሌ ላመልከው በፍቅሩ ስቦ ማርኮኛል ምሕረቱም ለእኔ ብዙ ነው ስለዚህ ወደድኩት ለእርሱ ተገዛሁለት (2x) አዝ፦ ፍቅሩን ቀምሻለሁ ምሕረቱን አይቼዋለሁ ድንቅ ነው በሕይወቴ ያረገዉ መድኃኒቴ ኦ ኃያል ሥሙን ኢየሱሴን ልባርከው ምሕረቱን አይቻለሁ (2x) ላመልከው ፈቅጃለሁ ድንቅ ነው በሕይወቴ (2x) ያረገው መድኃኒቴ ከእንግዲህ ፍቅሩ ማርኮኛል ሕይወቴን ሰጥቼዋለሁ ሌላ ማንም አይገዛኝም ለኢየሱስ ተለይቻለሁ በጣም ደስ ይለኛል የአምላኬ/የጌታዬ ፍቅር ገዝቶኛል (2x) አዝ፦ ፍቅሩን ቀምሻለሁ ምሕረቱን አይቼዋለሁ ድንቅ ነው በሕይወቴ ያረገዉ መድኃኒቴ ኦ ኃያል ሥሙን ኢየሱሴን ልባርከው ምሕረቱን አይቻለሁ (2x) ላመልከው ፈቅጃለሁ ድንቅ ነው በሕይወቴ (2x) ያረገው መድኃኒቴ እኔስ ፍቅሩን አይቻለሁ በድካም ቢሆን በብርታት ኢየሱስ ሁሌም ሕያው ነው ወዳጄ ወረት የለበት ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብለው ያረካኛል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection