Song Lyrics

መች እረሳሁ

Daniel Amdemichael
Mogninet Hono Ayidelem
አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ? ሁሉንም አስታውሳለሁ ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ ማዳንህን አይቻለሁ እጆቼን ላንሳ ላክብርህ ምሥጋናዬን ተቀበለው ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ ኧረ እንደርሱ ያለ ማነው? የራራልኝ በድካሜ ኃይል የሆነልኝ አቅሜ ጐኔ ቆሞ ያበረታኝ ማን ነበረ ከአንተ በላይ? አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ? ሁሉንም አስታውሳለሁ ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ ማዳንህን አይቻለሁ እጆቼን ላንሳ ላክብርህ ምሥጋናዬን ተቀበለው ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ ኧረ እንደርሱ ያለ ማነው? ከንፈሮቼን ቀባሃቸው ጠላቶቼ እያየ ዓይናቸው ዝማሬ በአፌ ጨምረሃል አመልክህ ዘንድ ይገባኛል አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ? ሁሉንም አስታውሳለሁ ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ ማዳንህን አይቻለሁ እጆቼን ላንሳ ላክብርህ ምሥጋናዬን ተቀበለው ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ ኧረ እንደርሱ ያለ ማነው? ሁሉም አልፎ እዚህ መድረሴ በአንተ እንጂ መች በራሴ? ክብር ለአንተ እሰጣለሁ ሁልጊዜ እዘምራለሁ አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ? ሁሉንም አስታውሳለሁ ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ ማዳንህን አይቻለሁ እጆቼን ላንሳ ላክብርህ ምሥጋናዬን ተቀበለው ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ ኧረ እንደርሱ ያለ ማነው? ልቤን ፍፁም ደስታ ሞላው የአንተ መሆኔን ሳስበው ብዙ ሰላም በዝቶልኛል ከአንተ እጅ ማን ያወጣኛል? አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ? ሁሉንም አስታውሳለሁ ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ ማዳንህን አይቻለሁ እጆቼን ላንሳ ላክብርህ ምሥጋናዬን ተቀበለው ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ ኧረ እንደርሱ ያለ ማነው?
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection