Song Lyrics

ሰላም

Daniel Amdemichael
Mogninet Hono Ayidelem
በአምሳልህ የተሠራ ይሄ ሰው ክቡር ነው መራብ መሰደዱ መሞቱ ለምን ነው? ምድራችንን ማራት እባክህ አምላካችን ንስሃ እንገባለን በፊትህ ሁላችን አዝ፦ ሰላም (4x) ለምድራችን ስለ አባቶች በደል ማረን እንላለን ስለ ልጆች በደል ማረን እንላለን ጦርነት ከምድር ጩኸት ዋይታው ይብቃ ጨለማችን በርቶ በሰላም ይተካ አዝ፦ ሰላም (4x) ለምድራችን (2x) የሰላሙን አየር ሁሉም ተጠምቶታል ጦርነት ስደትን ጆሮው ሰልችቶታል የሰላም አለቃ ሁሉም በእጅህ ነው ምድራችንን ማራት ሰላሟ በአንተ ነው አዝ፦ ሰላም (4x) ለምድራችን ትምክህት እልሃችን ይራቅ ከእኛ ይጥፋ ፍቅር መተሳሰብ በምድራችን ይስፋ ጦርነትን ሻረው ቀስቱንም ስበረው ሰላም ለሰው ልጆች ባይበሉም ጥጋብ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection