Song Lyrics

አለቴ ነው

Daniel Amdemichael
Mogninet Hono Ayidelem
ምሕረቱ ገንኖ በእኔ ላይ መልካም የሆነውን ቀን እንዳይ ጨለማዬን ሁሉ አብርቶአል ሃዘን ትካዜም ከእኔ ርቋል አንደበቴን ልክፈት ልናገር ያደረገልኝን ድንቅ ነገር መልካምነቱ ህሉ ይሰማ በእርሱ ዘንድ ዓይኖርም ጨለማ እርሱ የእኔ ወዳጅ እርሱ የእኔ እረኛ ( ለምን እሰጋለሁ ለምን ልቤ ይፍራ ዓለቴ ነው ጌታዬ ጽኑ ነው መሠረቴ እኔ ክፉን አልፈራም ኢየሱስ አለ በሕይወቴ ሃላፊው እርሱ ነው በእኔ ላይ ልረፍ እንጂ እኔ ምን አሰጋኝ? ብጨነቅ ባወጣው ባወርደው አንድም የለም የምጨምረው ታማኝ ነው የእኔ እረኛ የማይደክም ከቶ የማይተኛ ሃሣቤን በእርሱ ላይ እጥላለሁ ይረዳኛል አምኜዋለሁ በቸርነቱ እጄን ይዞ ትላንትናን እንዳሳለፈኝ ለዛሬውም አምላኬ አለልኝ ለምን ልፍራ ምን አስጨነቀኝ? ምሕረቱና ቸርነቱ ሁልጊዜ ይከተሉኛል አይተወኝም ለዘለዓለም ኢየሱሴ ቃል ገብቶልኛል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection