አዝ፦ ከእናቴም ከአባቴም ይልቅ የሚጠጋጋኝ ዘመዴ ኢየሱስ ነው መከታ ለእኔ አፍቃሪ የልብ ወዳጄ (2x) ፍቅሩን ሳስብ ይደንቀኛል ለእኔ ያሳየው ምህረቱ ባወራው ባወራው አያልቅ ችሎኝ አለሁ በቤቱ ትዕግሥቱ እጅግ ብዙ ነው አይሰለችም ይሸከማል መልካም የበጐች እረኛ እንደ እርሱ ከየት ይገኛል አዝ፦ ከእናቴም ከአባቴም ይልቅ የሚጠጋጋኝ ዘመዴ ኢየሱስ ነው መከታ ለእኔ አፍቃሪ የልብ ወዳጄ (2x) ውድ ነው ለእኔ ጌታዬ ዕንቁና ወርቅን ያስንቃል ጠረኑ ከሩቅ የሚስብ መዓዛውም ደስ ያሰኛል ፍቅር አለው ልብ የሚያረካ ወዳጄ ወረት አያውቅም ነፍሱን ስለ እኔ ለውጧል ፍቅሩን በሞት ገልጾልኛል አዝ፦ ከእናቴም ከአባቴም ይልቅ የሚጠጋጋኝ ዘመዴ ኢየሱስ ነው መከታ ለእኔ አፍቃሪ የልብ ወዳጄ (2x) ታማኝ ነው የማይለወጥ ጓደኛ ጊዜ አይቶ የማይርቅ የዘለዓለም ሕይወት ዋሴ ኢየሱስ አዳኝ ለነፍሴ ድቅድቅ ጨለማን የሚገፍ ብርሃን ይሁን ይብራ ያለ ድንቁ የሰላም አለቃ ኧረ እንደ ጌታ ማን አለ አዝ፦ ከእናቴም ከአባቴም ይልቅ የሚጠጋጋኝ ዘመዴ ኢየሱስ ነው መከታ ለእኔ አፍቃሪ የልብ ወዳጄ (2x)