Song Lyrics

የጌቶች ጌታ

Daniel Amdemichael
Beante Birtat
በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ ስሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው እንደ ጸሐይ ያበራል ማነው የሚመስለው ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው አለም ሁሉ ይወቀው በሰማይም በምድር ፈቺ ያልተገኘለትን ድንቁ ጌታ ኢየሱስ ነው የፈታው ማህተሙን በረከት ይገባዋል ክብር ይሁን ለንጉሡ ስግደትም ይገባዋል ስግደት ይሁን በፊቱ አዝ፦ በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ ስሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው እንደ ጸሐይ ያበራል ማነው የሚመስለው ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው አለም ሁሉ ይወቀው እልፍ አእላፍት መላእክቶች ቅኔን የቀኙለታል ሽማግሌዎች ፊቱ ወድቀው ይሰግዱለታል በረከት ልትቀበል ይገባሃል ይሉታል ምስጋናና ውዳሴ ለእርሱ ያቀርቡለታል አዝ፦ በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ ስሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው እንደ ጸሐይ ያበራል ማነው የሚመስለው ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው አለም ሁሉ ይወቀው ሃያል ነው ክንደ ብርቱ የሚመስለው የሌለ በእውነት በጽድቅ የሚፈርድ ዲያቢሎስን የጣለ የዘላለም ንጉስ ነው ኢየሱስ የከበረ በሰማይም በምድር እጅጉን የገነነ አዝ፦ በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ ስሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው እንደ ጸሐይ ያበራል ማነው የሚመስለው ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው አለም ሁሉ ይወቀው በአምባ ላይ ፈረስ ጌታችን ይቀመጣል ጠላቱን ያሸንፋል አመፀኛውን ይቀጣል በክብሩ የተነሳውን በክንዱ ያደቀዋል የጌቶች ጌታ ኢየሱስ ለዘላለም ይነግሣል አዝ፦ በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ ስሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው እንደ ጸሐይ ያበራል ማነው የሚመስለው ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው አለም ሁሉ ይወቀው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection