Song Lyrics

ፍቅሩ ማርኮኛል

Daniel Amdemichael
Beante Birtat
አዝ፦ አልሰለችም ሁልጊዜ ጌታን ባርከዋለው ምህረቱ በኔ ላይ ነው ይህን ተረድቻለው ( 2x) ኦ ፍቅሩ ማርኮኛል ( 2x) ተማርኬያለው በኢየሱስ ሰላም አግኝቻለው ( 2x) ምህረቱ እጅግ ብዙ ነው ቸርነቱ ወደር የለው ከአመት አመት አይለወጥ ፍቅሩ ቋሚ ሁሌ ጽኑ ነው ውድ ነው ኢየሱስ ጌታ እንደሱ ያለ ከየት አገኛለው በኔ ላይ የገለጸውን መውደዱንም ተረድቻለው አዝ፦ አልሰለችም ሁልጊዜ ጌታን ባርከዋለው ምህረቱ በኔ ላይ ነው ይህን ተረድቻለው ( 2x) ኦ ፍቅሩ ማርኮኛል ( 2x) ተማርኬያለው በኢየሱስ ሰላም አግኝቻለው ( 2x) የአምላኬ ትህትናውን የዋህነቱን አይቼ አብሬው ልኖር ወሰንኩችኝ ልከተለው ሁሉንም ትቼ ወደሱ መጥቶ ማን አፍሯል ሚስኪኑ ሰው ቀን ወቶለታል ሀዘኑ ማቁ ተቀዶ እንባው ታብሶለት ይኖራል አዝ፦ አልሰለችም ሁልጊዜ ጌታን ባርከዋለው ምህረቱ በኔ ላይ ነው ይህን ተረድቻለው ( 2x) ኦ ፍቅሩ ማርኮኛል ( 2x) ተማርኬያለው በኢየሱስ ሰላም አግኝቻለው ( 2x) ድንቅ የሆነለት ይዘምር አይቆጠብ ማዳኑን ያውራ ብቻውን ተአምር የሚያደርግ እንደ እግዚአብሔር የለምና አንደበቶች ይከፈቱ የንጉሱን ምስጋና ያውሩ ሰማይን ምድርን ለሰራው ሰወች ሁሉ ክብርን ይስጡ አዝ፦ አልሰለችም ሁልጊዜ ጌታን ባርከዋለው ምህረቱ በኔ ላይ ነው ይህን ተረድቻለው ( 2x) ኦ ፍቅሩ ማርኮኛል ( 2x) ተማርኬያለው በኢየሱስ ሰላም አግኝቻለው ( 2x) የአምላኬ ትህትናውን የዋህነቱን አይቼ አብሬው ልኖር ወሰንኩችኝ ልከተለው ሁሉንም ትቼ ወደሱ መጥቶ ማን አፍሯል ሚስኪኑ ሰው ቀን ወቶለታል ሀዘኑ ማቁ ተቀዶ እንባው ታብሶለት ይኖራል አዝ፦ አልሰለችም ሁልጊዜ ጌታን ባርከዋለው ምህረቱ በኔ ላይ ነው ይህን ተረድቻለው ( 2x) ኦ ፍቅሩ ማርኮኛል ( 2x) ተማርኬያለው በኢየሱስ ሰላም አግኝቻለው ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection