አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይተወኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ እጮሀለሁኝ እኔ አልታክትም እስኪጎበኘኝ ተስፋ አልቆርጥም እንባዬን ካይኔ እስኪያብስልኝ እጠብቃለሁ እስኪደርስልኝ ጌታ እስኪያየኝ (3x) አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይገባኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ እስኪ እንደሀና እንባዬን ላፍስስ መሪር ሀዘኔን በፊቱ ልግለፅ ጨካኝ እንዳይደል እኔ አውቀዋለሁ ከእግሩ ስር ሆኜ ልማፀነው ደጅ ልጥናው (3x) አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይገባኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ ፈተናው በዝቶ ቢያዝለኝም ለሰይጣን ሀሳብ እጄን አልሰጥም እርዳኝ እላለሁ በፊቱ ሆኜ ድንቅ እንዲሰራ በእርሱ ታምኜ በረድኤቴ (3x) አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይገባኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ እታገሳለሁ ምልስ ይሆነኛል ጌታ ጨክኖ መች ይተወኛል የልመናዬ ፅዋዬ ሞልቶ ይጎበኘኛል በጊዜው መጥቶ በቃ ብሎ (3x) አዝ፦ ለምን እንደዘገየ ለእኔ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፈፅሞ አይገባኝም ስጋዬን ልንከስ ልማፀነው ፀሎቴን ሰምቶ እስኪመልሰው ጌታ