አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (2x) ከልጅነት የተሸከመኝ እስከሽምግልና የሚመራኝ አሳዳጊ ይህ ወላጅ የሆነኝ ያለእርሱ ወገን ማነው ያለኝ አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (2x) ቢከፋኝ ቢደላኝ እርሱ ነው ሁልጊዜ ከጐኔ ማገኘው ከእናት ከአባት በላይ ወዳጄ ኢየሱስ ነው ተቆርቋሪ ለእኔ አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (2x) እግሬን ከጨለማ መልሷል በፍቅሩ ገመድ ውስጤን አስሯል ልዩ ነው ልዩ ነው ለእኔ በፍቅሩ ተማርካለች ነፍሴ አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (2x) ሕያው ነው ምንም አያረጅም ዘመን ሲያልፍ እርሱ አይለወጥም ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ታማኝነቱ ለእኔ ብዙ ነው አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም በጣም ተዋደናል አንለያይም (2x) በጣም ተዋደናል አንለያይም (2x)