Song Lyrics

የሕይወቴ ሚስጥር

የሕይወት ሚስጥር ሳይገባቸው ሲከተሉ ለእንጀራቸው አልተስማሙም ከአንተ ጋራ ተመለሱ ወደ ኋላ እኔስ በርቶልኛል መዳን ሆኖልኛል ሕይወት አንተ ብቻ ኢየሱስ የለህ አቻ አዝ፦ ምንም ላላገኝ ከአንተ ርቄ ላይሆንልኝ ጥሜ ላይረካ የዓለም ኑሮ ላይፈይደኝ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁኝ ኢየሱስ እንደ አንተ ለእኔ የሚሆን መቼም ቢሆን አላየሁኝ (2x) መድኃኒቴ አንተ ልዩ ነህ ማንም የለም የሚመስልህ ኢየሱስ ለእኔ መከታዬ ጋሻዬ ነህ ከለላዬ ከአንተ አልለይም ሌላው አይሆንልኝም የሕይወት ቃል አለህ ጥሜን ታረካለህ አዝ፦ ምንም ላላገኝ ከአንተ ርቄ ላይሆንልኝ ጥሜ ላይረካ የዓለም ኑሮ ላይፈይደኝ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁኝ ኢየሱስ እንደ አንተ ለእኔ የሚሆን መቼም ቢሆን አላየሁኝ (2x) ከአንተ ጋር ኑሮ ተመችቶኛል ኢየሱሴ አሙቆኛል በፍቅርህ ነው እኔን የሳብከኝ እስክሞት ድረስ የወደድከኝ በቃ ወስኛለሁ አንተን መርጫለሁ እርስቴ ነህ ብያለሁ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ አዝ፦ ምንም ላላገኝ ከአንተ ርቄ ላይሆንልኝ ጥሜ ላይረካ የዓለም ኑሮ ላይፈይደኝ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁኝ ኢየሱስ እንደ አንተ ለእኔ የሚሆን መቼም ቢሆን አላየሁኝ (2x) ኢየሱስ ሕይወቴን አብርተሃል እኔነቴን ለውጠሃል አልለይህም ወድሃለሁ ከአንተ ውጪ ጨለማ ነው ግዛኝ የእኔ ጌታ ልስገድ ጠዋት ማታ ነፍሴን የተቤዠህ አንተው ትሻሃለኛለህ አዝ፦ ምንም ላላገኝ ከአንተ ርቄ ላይሆንልኝ ጥሜ ላይረካ የዓለም ኑሮ ላይፈይደኝ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁኝ ኢየሱስ እንደ አንተ ለእኔ የሚሆን መቼም ቢሆን አላየሁኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection