አዝ፦ ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ ኢየሱሴ ለአንተ ተሰጥቻለሁ ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ (2x) ብዙ የከበሩ በምድር ላይ ሞልተው ታላቅ ነኝ ባዩን ልታሳፍረው እኔን መረጥከኝ ዓሣ አጥማጁን ሰው ኧረ ልዩ ነው ኢየሱሴ ፍቅርህ አታምደህ አይል አመራረጥህ ለእኔም ደረሰኝ ድንቅ ማዳንህ አዝ፦ ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ ኢየሱሴ ለአንተ ተሰጥቻለሁ ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ . (1) . ያልፍለት ለዚህ ሥጋዬ ቀን ቀን ስደክም መረቤን ጥዬ ምንም ላላገኝ በድካም ጥዬ አንተ ግን መጥተህ ተዓምርን ሰራህ መላው ሕይወቴን መገረም ሞላ ሥሜን ተግባሬን ኑሮዬን ቀየርክ አዝ፦ ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ ኢየሱሴ ለአንተ ተሰጥቻለሁ ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ ከኋላዬ ና ወድጄሃልሁ ለማዳን ሥራ መርጬሃልሁ ሰዎችን አጥማጅ አደርግሃልሁ . (2) . ጌታዬ እኔም ተረታሁ ከልብ ወደድኩህ ሕይወቴን ሰጠሁ እስከ ዘለዓለም አመልክሃለሁ አዝ፦ ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ ኢየሱሴ ለአንተ ተሰጥቻለሁ ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ . (3) . ትህትናህ ሳበኝ በኃይል በጉልበት አላስገደድከኝ አንተ ፍቅርህ ነው ያንበረከከኝ ልከተል ወሰንኩ ጥሩ ጌታዬ በነገር ሁሉ አንተን ታምኜ መረብ ታንኳዬን ሁሉንም ጥዬ አዝ፦ ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ ኢየሱሴ ለአንተ ተሰጥቻለሁ ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ (2x)