ሀሳቤ የልቤ ባይሞላ ያቀድኩት ነገር ባይሰካ ላመስግን ልተው ማማረሬን ያልከው ይሁን ጌታ ያ መልካም ነው ለእኔ አዝ፦ ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (2x) ችግሬ ረሃቤ ቢፀናም ቁስሌ ባይደርቅ ፈውሴ ቢዘገይ ከፈቀድከው ይሁን ማለት አስተምረኝ ጌታዬ ትግስት. (1) . አዝ፦ ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (2x) ጌታ ነህ ብትገል ብታድንም መከራካር ከአንተ ጋር አይበጅም (2) . ክፉን ሆነህ አይደለም ጨካኝ እንደ አላማህ ጌታ የምትረዳኝ አዝ፦ ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (2x) አንተ ያልከው ይሻለኛል የእራሴማ መቼ ያዋጣኛል ትርፉ መላላጥ መቁሰል ነው ለአንተ ሀሳብ ጌታ መገዛት ጥሩ ነው አዝ፦ ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (2x) በሥራው ሁልጊዜ ጻድቅ ነህ ተሳስተህስ መቼ ታውቃለህ ሀሳቤን በሀሳብህ ጠቅልለው ምኞቴንም ኢየሱስ እንደ ቃልህ አርገው አዝ፦ ከአንተ ጋር መስማማት ይሻላል መማረር ማኩረፍ ምን ያዋጣል ፈቃድህ ይሁን ማለት መልካም በጊዜው ነገር ውብ ይሆናል (2x)