Song Lyrics

ችላ አትበል

አዝ፦ ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ አያዋጣም እዚም እዚያም መረጋገጥ እንዲሁ መዋተት ትርፉ መሞት ነው ተው ወንድሜ አያዛልቅ በኃጢአት መዋኘትህ ወስነህ ተቀበል ጌታን በልብህ ኃጢአት አያባብለህ ጨክነህ ተወው ተወው ይቅርብህ አዝ፦ ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ የዓለም ኑሮ እሽኮለሌው እያሳሳቀ ወደ ሞት ነው ይልቅ መቃ ዛሬ ወስን ሞት እንደው ቀጠሮ የለው በሕይወትህ ሰላም አግኝ እረፍትን ዲያቢሎስ ሲጠራ ዛሬ ነገ አትበል ስጠው ልብህን አዝ፦ ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ ሀብት ቢሞላ ቢትረፈረፍ ለነፍስ አንድም ጠብታ የለው አንተነትህን የሚያረካ ካለ ኢየሱስ ሁሉም ዘበት ነው እረኝነቱ ሥር መጥተህ ተጠለል ኢየሱስን ምረጠው ለነፍስ ለሥጋህ ሌላ ሌላ አትበል አዝ፦ ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ ና ወደ እርሱ ጌታ ይመጣል አንተነትህን ይለውጣል በአዲስ ሕይወት በአዲስ ኑሮ ልብህን ደስታ ይሞላል ሰላምህ እንደ ወንዝ ሞልቶ ይፈሳል ዋጋ አትከፍልበትም ወስን ወንድሜ ወስን ጌታ ይሻላል አዝ፦ ኧረ ተው ወንድሜ ችላ ችላ አትበል ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተል ኧረ ተይ እህቴ ችላ ችላ አትበይ ሕይወት ቀልድ አይደለም ይብቃ ዝላዩ ጌታን ተከተይ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection