በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምህረቱን በእኔ የገለጠው እግዚአብሔር እግዚአብሔር ታማኝ አምላክ ነው እግዚአብሔር እግዚአብሔር መልካም አምላክ ነው (*2) ሀይል የሱ ነው ክንዱም የበረታ እንደ ሰው አይሸበርም አይዝልም የኔ ጌታ በሚነዋወጠዉ ንፋስ ማዕበሉ ሀሳብ ይገዛል ከልካይ የለዉም ቃሉ በሞት ጥላ መካከል በሚያስፈራው መንገድ ከእኔ ጋር ሚሄድ እየደገፈ እየመራ አብሮኝ ከኔ ጋራ (*2) ሀይል የሱ ነው ክንዱም የበረታ እንደ ሰው አይሸበርም አይዝልም የኔ ጌታ በሚነዋወጠዉ ንፋስ ማዕበሉ ሀሳብ ይገዛል ከልካይ የለዉም ቃሉ ጌታ ብርሃኔ ነዉ የሚያስፈራኝ ማነው እርሱ መድሀኒቴ ነዉ የሚያስደነግጠኝ ማነው (*2) ለነገም ቢሆን በእርሱ እታመናለሁ እስከመጨረሻው ልያደርሰኝ ታማኝ ነው ለነገም ቢሆን በእርሱ እደግፋለሁ እስከመጨረሻው ልያደርሰኝ ታማኝ ነው ጌታ ብርሃኔ ነዉ የሚያስፈራኝ ማነው እርሱ መድሀኒቴ ነዉ የሚያስደነግጠኝ ማነው (*3) ለነገም ቢሆን በእርሱ እታመናለሁ እስከመጨረሻው ልያደርሰኝ ታማኝ ነው ለነገም ቢሆን በእርሱ እደግፋለሁ እስከመጨረሻው ልያደርሰኝ ታማኝ ነው(*2)