መንፈስ ፡ቅዱስ ከኔ ጋር ያለዉ እርሱ ብቻ ነው ሚያኮራ ሌላ ማን አለ መንፈስ ፡ቅዱስ በውስጤ ያለዉ እርሱ ብቻ ነው ሚያስመካ ሌላ ምን አለ ሌላ ምን አለ (፬) ሌላ ማን አለ (፬) በኃይሌ አይደለም ወይም በብርታቴ ፡ መውጣቴ መግባቴ ያማረው ሕይወቴ በመንፈሱ እንጂ ሁሉን በሚችለው ደካማውን ብርቱ ብርቱ በሚያደርገው አለኝ እውነቱን ሚያስተምረኝ አለኝ መልካሙን ሚያሳየኝ በለመለመ መስክ የሚያሳድረኝ በረፍትም ዉሃ ዘንድ ሁሌ ሚመራኝ ፡ ያጽናናኛል ይደግፈኛል ፡ በጐነቱን ይገልጥልኛል መካሪዬ ነው አለኝታዬ ፡ ዘልቆ ሚኖር ውስጤ ጟዳዬ አለኝ እውነቱን ሚያስተምረኝ አለኝ መልካሙን ሚያሳየኝ በለመለመ መስክ የሚያሳድረኝ በረፍትም ዉሃ ዘንድ ሁሌ ሚመራኝ በቅዱሱ መንፈስህ እመካለሁ በቅዱሱ መንፈስህ እኮራለሁ በቅዱሱ መንፈስህ እጽናናለሁ ከቅዱሱም መንፈስህም እማራለሁ እኮራለሁ (፬) እመካለሁ (፬)