Song Lyrics

ኢየሱስ

ብዙ ቃላት ባይኖር ልቤን የሚያብራራ መንፈሴ ቅርብ ነው ፍቅሬን የሚያስረዳ ስምህን ስጠራ እየሱሴ ስልህ ነፍሴ ትፈሳለች አምላኬ በፊትህ ኢየሱስ (12* ) እየሱሴ ብዬ ስምህን ጠርቼ በፍቅር በምህረትህ በአንተ ተመክቼ እየሱሴ ብዬ ስምህን ጠርቼ በሀይል በጥበብህ በአንተ ተመክቼ አመለጥኩ ከሞት አተረፍክ ነፍሴን ስምህ ድንቅ ነው ደረቁን የሚያርሰው ከመጠማት ወሬ ሰፈር የሚያወጣው ከፍቅርህ አጠጣኸኝ አልሻም ካንተ ውጭ ከውስጤ አፍልቀሀል የህይወት ውሃ ምንጭ ኢየሱስ (12* ) እየሱሴ ብዬ ስምህን ጠርቼ በፍቅር በምህረትህ በአንተ ተመክቼ እየሱሴ ብዬ ስምህን ጠርቼ በሀይል በጥበብህ በአንተ ተመክቼ አመለጥኩ ከሞት አተረፍክ ነፍሴን(3*)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection