በተጣለች አለም መሃል የዘመትን የምንለመልም ዘዉትር እየሞትን ትውልድን ለማትረፍ ከዘላለም ቁጣ የመዳንን ወንጌል ይዘን የምንወጣ… (ምስክር ነን እኛ!) [አዝ] ጥበባችን ሁሉ ሞኝነት ‘ሚመስል የእግ’ዚአብሔርን ፍቅር ለሰው የምንስል ሲረግሙን መራቂ ላሳዳጆች ፀላይ መልካም የምንመኝ ጠላቶቻችን ላይ… ምስክር ነን እኛ! [አዝ] ዋጋችን በሰማይ ሀይላችን በፀሎት ምንዳን የማንሻ ለምድር አገልግሎት ኢየሱስን ይዘን የማናቀረቅር መንገዳችን ቀና እርምጃችን ፍቅር… ምስክር ነን እኛ! [አዝ] “የምን ደርሶ አዋቂ የምን ደርሶ አቡን አጉል ጠበቃዎች…” ሲሉ ቢያዋክቡን ቢያላጉን በጥፊ ቢያዳፉን በጡጫ በስል ምላሳቸው ብንሆን ማላገጫ… ምስክር ነን እኛ! [አዝ] በሞት ጥላ ግርዶሽ ተከበው ለኖሩ ብቃት አጣን ብለው አጋዥ ለሚጠሩ የምስራች ይዘን ለህዝቡ ወጥተናል ዛሬም እንላለን ኢየሱስ ያድናል!! (ኢየሱስ ያድናል)