ላንተ ክብርን ሳቀርብ ስሰዋ ምስጋና በልኬ ሰፍቼ እንዳላሳንስህ እፈራለሁና ደስ በሚያሰኝህ አይነት እንዳመልክህ አንተን አስተምረኝ እንዳውቅህ በልክህ ልወቅህ ጌታዬ ደስ ተሰኝብኝ በቃየን መሰዊያ መስዋዕቴ አይገኝ [አዝ] ነፍሴ ሀሴት አድርጋ ዝማሬ ‘ሰማለሁ ከሚያመልኩህ ጋራ አብሬ አምልኬአለሁ “አባት አልልህም” ሲሉህ አጅቤኣለሁ ግን ካንተ ወዲያ አባት ከየት አገኛለሁ? [አዝ] ልወቅህ ጌታዬ ልሁን ባንተ ቅጥር ባንተ ድልን ሳገኝ ጦሬን እንዳልቆጥር 2x ላንተ የማቀርበው ንጹህ መስዋዕቴ ምሉዕ እንዲሆንልኝ ቢሳካ ምኞቴ ልቦናዬን አብራው ክብርህን እንዳየው ከስጦታ በላይ ሰጪውን ልለየው! [አዝ] ትወቅህ ይኽች ልቤ በቃልህ አሙቃት እንዳሻት እንዳትሆን ከጥፋት ጠብቃት 2x ሁሌ እንደለመድኩት ስላደረግከው ድንቅ ወይም ድል ለማግኘት ስለከበበኝ ጭንቅ አይሁን ጌታዬ ሆይ ስብከቴን ጨምቄ ላምልክ እንጂ ገብቶኝ ክብርህን አውቄ