Song Lyrics

የእንጨትነት ሕይወት

Yenchetinet Hiwot

Alula Getahun
Asyizegn Meskelun
ልፋ ያለው እንጨት እድሉ የጠመመ ባሬላ ተብሎ እየተሰየመ ያንን ኩንታል ድንጋይ እየተሸከመ - ደግሞ ሌላው እንጨት የ'ንጨት እድላሙ መስቀል ነህ ተብሎ ተሰይሞ ስሙ አላፊ፣ አግዳሚ እ'ሱን እንዲያስሙ ቀሳውስትን ቀጥሮ በተቀባ ስሙ አንዱ የ'ንጨት ባሪያ ሌላው የ'ንጨት ንጉስ ይሄ መሬት ሲስም ያንኛው ሲኮፈስ 2x የተቀባው እንጨት ካ'ናት ይሰቀላል ሌላ ታናሽ ረግጦ በእንጨት መሰላል ካ'ናት ጋር እስኪደር አንዱ ባ'ንዱ ልቆ በእንጨት ገበያ እንጨት በ'ንጨት ደምቆ አንዱ የ'ንጨት ባሪያ ሌላው የ'ንጨት ንጉስ ይሄ መሬት ሲስም ያንኛው ሲኮፈስ 2x ቢያቃጥሉት አመድ ቢቆርጡትም ጉቶ ቢለበለብ ከሰል ጉቶነቱን ትቶ ለያይተነው እንጂ ስሙን ሸልመነው ከንቱ ተሰባሪ እንጨት ያው እንጨት ነው አንዱ የ'ንጨት ባሪያ ሌላው የ'ንጨት ንጉስ ይሄ መሬት ሲስም ያንኛው ሲኮፈስ 2x ምንም አንዱ ቢገን ሌላው መሬት ቢልስ መፈራት ያለበት የ'ንጭቶቹ ጌታ በ'ሳት የሚመልስ 2x
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection