Song Lyrics

ገናና

Genana

Alula Getahun
Asyizegn Meskelun
አቤቱ በስራህ ስምህ የገነነ በሰማይ በምድር የተመሰገነ፤ ያንተን ህልውና የሚጠራጠሩ በእጆችህ ስራ ከምክንያት አጠሩ። ገናና ነህ ዝነኛ የፍጥረት ምንጩ መገኛ ጅማሬህን አናውቀው ፍፃሜህን አናውቀው በ'ድሜያችን በምናውቅህ ስራህን እናድንቀው! ጥበብህ ሰላምህ ላ'ለም የሚበቃ ድንቅ፥ መካር፥ ኃያል የሰላም አለቃ፤ መላእክት ባንድ ላይ ቅዱስ ነህ ይሉሃል የለም የሚመስልህ ከሚኖሩት መሃል። [አዝ] ባ'ንተ ያለን ሞኝነት ከእውቀት ሚዛን ቢጣል ባ'ለም ካሉ ጥበቦች ብዙ ርቀት ይበልጣል፤ ያ'ንተ ስራ ሲታወጅ በምድር ላለ አካል ምስጋናህ በህዝብህ ላይ እንዳ'በባ ይፈካል። [አዝ] ስ'ሰጠን ተመስገን፥ ስታስቀር ተመስገን ያልነውን ነው እንጂ ያልከውን አትነፍገን፤ ከምናውቅህ በላይ ስምህ ከፍ ያለ ነው አፍረንብት አናውቅም አንድ ጊዜም ጠርተነው። በክብርህ የመጡን እግዚአብሔር ተዋጊ ከቤትህ የጠፉን እግዚአብሔር ፈላጊ፤ እግዚአብሔር ኃይለኛ እግዚአብሔር ከፍታ እግዚአብሔር አምባችን እግዚአብሔር መከታ! እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር እግዚአብሔር አንተን ነው ዘውትር የምንጠራው የትኛው ጀግና ነው አንተን የሚያስፈራው!
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection