Song Lyrics

አትመጣም ወይ?

Atimetam Wey

Alula Getahun
Asyizegn Meskelun
አትመጣም ወዪ ኧረ አትመጣም ወዪ ዛሬም አሻቅበናል ወደሰማዪ አትመጣም ወዪ ዉዴ መምጫህ ናፈቀን የከለለህ ደመና መልክህን ደበቀን! ጥንት የተሰራው ስራ ዛሬ የሆነ መስሎ በፊታችን ትይዩ መሰቀልህ ተስሎ አንተን አንተን እያልን ዛሬም እዛ’ው ቆመናል ልክ እንደሄድከው ሁሉ ብትመጣልን ምናል? [አዝ] ዳግም መምጫህ ናፍቆናል የፍጥረትህ ማረፊያ ነፃ የምንወጣበት ከአለም ትግል ልፊያ እመጣለሁ እንዳልከን እንደቃልህ ድንገት ና በመምጣትህ ገላግለን ካ’ለማዊ ፈተና! [አዝ] የስጋ ኑሮ ታከተን የእድሜ ሙሉ ድካም በምናገኘው ሁሉ ልባችን ከቶ አይረካም ትናንት ቆመናል ባልነው ዛሬ ጠልፎን ወድቀናል ኢየሱስ ቶሎ ናልን ሁሉ መልካም ይሆናል! [አዝ] የኛን ጉጉት የሚያዩ ጌታ በዚህ ነው ቢሉን የመምጫህ ቁርጡን ጊዜ አንድም ባናውቀው ውሉን በከንቱ ጓዳ ሳይሆን ዙሪያህ ሆኖ ደመና አለምን ያናውጣል የመመለስህ ዝና! [አዝ]
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection