እንዳላየ በሚያልፍበት የከበበኝ ይህ ሁሉ ሰው በሞት ጥላ ስር ካለሁበት እግዚአብሔር ነው የደረሰው! [አዝ] “በችግሩ ‘እግዚአብሔር ሆይ’ ለምን ይላል በደረቁ” “አላየዉም አልሰማዉም” ብለው ሳቁ ተሳለቁ! አምላኬ ግን አልሰጠኝም ለሳቁብኝ አሳልፎ ድካሞቼን አስወገደ እንደጊዜው አረጋግፎ! [አዝ] ብዙ ሰልፎች በነፍሴ ላይ ሲንጓደዱ እየዋሉ አልፎኝ ሄዷል ብዙ ጊዜ ከንፈር መጦ ሰው ላመሉ! “ማን ያድነኝ?” ባልኩት ጩኸት ይነግዳል ግብዝ መንጋ በዙሪያዬ ካሉ እጆች የ’ሱ ብቻ ተዘረጋ! [አዝ] ትናንትና በደም ገንዝብ ኑሮ አቁመው የደመቁ አሁን የሉም ጠፋፍተዋል እንደጤዛ አየደረቁ! ለምለም መሳይ የጊዜያዊ መንገዶችን በለመዱ ዛሬ አልቀናም ተምሬያለሁ እሄዳለሁ በመንገዱ! [አዝ] የሰው ልቡ ይታበያል መነሻዉን እየረሳ ቀን ሲያልፍለት እድል ሲያገኝ የወደቀን አያነሳ! በመከራ መሸሸጊያ በክፉ ቀን የሚጠራ እግዚአብሔር ነው ፈጥኖ ደራሽ እንደጊዜው የሚሰራ!