ከህግ በታች ያለን በተጣለ ስጋ እዳን የሚከፍል የበቃን ፍለጋ ማን ያድነን ብለን ስንጠብቅ ተዓምር ማህተሙን ፈቶ በራሱ ሞት ‘ሚምር አላውቅም ከሰው በደል በላይ አላውቅም የሰው ድካም አሞት አላውቅም በፅድቅ ሆኖ ሳለ አላውቅም ለኃጥአን የሚሞት… ለካ ግን አለ ስሙ ማይከስም ሞቶ የተነሳ ሰማሁ አንድ ስም [ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x ለገዛ ፍርዳቸው ምትክ ልሁን ባለ ለሚሳለቁበት መስቀል ላይ እንዳለ ላደረጉት ሁሉ ምህረት የሚለምን አንዱን ብቻ ሰምተን እንዲህ የተገረምን አላውቅም እንዲህ ያለ ነገር አላውቅም ድንቅ የሆነ ወሬ አላውቅም በጆሮዬ አልገባም አላውቅም ነበር እስከዛሬ…. ለካ ግን አለ ባለይቅርታ ሰማሁ አንድ ስም እንዲ ያለ ጌታ…. [ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x ድኩም መስሎ መምጣት ታላቅ ክብሩን ትቶ ክብርን ከጠገበ አልጠብቅም ከቶ እንዴት ያለ ንጉስ እንዴት ያለ ኃያል ሀይሉን በገዛ እጁ ትቶ ፍዳን ያያል? አላውቅም በዙፋን ላይ ሳለ አላውቅም የደካማ ወዳጅ አላውቅም ክብሩን ትቶ ሚወርድ አላውቅም ያላንዳች አስገዳጅ ለካ ግን አለ ለኛ የሚገደው አንድ ስም አለ ፍርዱን የናደው [ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ … ኢየሱስ] 3x