ያልተቀበልነው ምን ምን አለ? ሁሉ በርሱ ነው ሞላ፥ ጎደለ ለገባው ቃሉ የታመነ እግዚአብሔር ነው የገነነ እግዚአብሔር ብቻ ነው የመስጠት ልኩ ተቀብላችሁ ክብሩን አትንኩ ቢጎል ቢሞላ ለነፍስ ዋስትና ሲጠማን ምንጭ ነው ሲርበን መና! [አዝ] ደከመኝ አይል አጋዥ አይሻ በራሱ ሙሉ የራሱ ጋሻ ታክቶት አላየን እንደዛለ ሰው አንዴም አልሰማን ጉልበቱ ሲያንሰው! [አዝ] ይኼ ማን ነው ባህር ያቆመ የህዝቡን ማዳን የፈፀመ? ኧረ ይህ ማን ነው የማዕዘን አለት ፍጥረታት ሁሉ የሚገዙለት? በ'ፍኙ የሚሰፍር ያሉትን ቀላያት በምድርም ያሉ የሰማይም ሰማያት፤ በኃይል የታሰሩትን ፈቶ የለቀቀ የሚጋፉን ዓለማት ሰብስቦ ያረቀ! ጫንቃችን ላይ በዝቶ የኃጢያት እዳችን በፍርድ ስር ሳለን መውጫ መንገዳችን፤ የብርሃን መገኛ የሰው ልብ ያበራ የፍጥረት ፈጣሪ ማዳኑን የሰራ! እግዚአብሔር ብቻ ነው የመስጠት ልኩ ተቀብላችሁ ክብሩን አትንኩ ቢጎል ቢሞላ ለነፍስ ዋስትና ሲጠማን ምንጭ ነው ሲርበን መና! በ'ፍኙ የሚሰፍር ያሉትን ቀላያት በምድርም ያሉ የሰማይም ሰማያት፤ የብርሃን መገኛ የሰው ልብ ያበራ የፍጥረት ፈጣሪ ማዳኑን የሰራ! ኢየሱስ ክርስቶስ መድኅኒተ አለሙ በፍጥረት ሁሉ ፊት ገናና ነው ስሙ። 2x