የልብ ሰው ከፈለክ እኔ አለው ስትጠራኝም መልሴ እነሆኝ ነው የልብ ሰው ከፈለክ እኔ አለው ስትጠራኝም መልሴ አለሁኝ ነው ቆይልኝ ህይወት ሆይ ቆይልኝ ከቤቴ የራስህ አይደለም ወይ አደባባይ ማጀቴ ስትቆይ የቆየ ጥያቄ ይመለሳል በጨዋታ መሃል ችግሬ ይነሳል ስትቆይ የቆየ ጥያቄ ይመለሳል እየተጫወትን ድካሜ ይነሳል መጥተህማ አትመለስም መጥተህማ ደጅ አትቆምም መጥተህማ እንግዳዬ መጥተህማ ማረፊያዬ መጥተህማ አልፎልኝ መጥተህማ እኔ ቤት በጭራሽ አትመለስም ሳታድር ሳትውልበት መጥተህማ አትመለስም መጥተህማ ውጪ አትቆምም መጥተህማ እንግዳዬ መጥተህማ አበባዬ መጥተህማ አልፎልኝ መጥተህማ እኔ ቤት በጭራሽ አትመለስም ሳታድር ሳትውልበት ቆይልኝ ህይወት ሆይ ቆይልኝ ከቤቴ የራስህ አይደለም ወይ አደባባይ ማጀቴ ቆይልኝ ኢየሱስ ቆይልኝ ከቤቴ የራስህ አይደለም ወይ አደባባይ ማጀቴ አረፍ በል ወዳጄ ብሎ ሲያጥብ እግሮችህን እንጎቻ ሲያዘጋጅ ሲያርድ የሰባውን ቸርነትህ በዝቶ ቤቱ ስትቆይለት የቆየ ጥያቄውን ሳራን አሰብክለት ማልዶ እንደተነሳ ሊሰዋ አንድ ልጁን ተብሎ እንደተጠራ የእግዚአብሔር ወዳጁ በተሻለው ኪዳን ከመጣህ ወደ እኔ እኔ በአንተ ልኖር አንተም ልትኖር በእኔ ደስታዬ አይደለም ወይ ብትቆይልኝ ቤቴ የማትወደው ሁሉ ይወጣል አባቴ ብርቄ አይደለም ወይ ያንኳኳኸው ደጄን ልቤ እንደምትሻው ይሆናል ወዳጄ ቆይልኝ ህይወት ሆይ ቆይልኝ ከቤቴ የራስህ አይደለም ወይ አደባባይ ማጀቴ ቆይልኝ ህይወት ሆይ ቆይልኝ ከቤቴ የራስህ አይደለም ወይ አደባባይ ማጀቴ