Song Lyrics

ይቅርታዬ ነህ

Helina Dawit
Special Edition
የክብር ልብሷን ለብሳ እንደ ቆመች ንጉሱ ፊት የወርቁንም ዘንግ እንደ ነካች ጥያቄዋን እንደመለሰላት እኔም ኢየሱስን ለብሼ አብ ፊት ሞገስ አገኘው አባባት ማለት ድፍረቴ ተመለሰልኝ ወደ ህይወቴ አባቴ የማለት እምነቴ ተመለሰልኝ ወደ ቤቴ የመማጸኛ ከተማዬ ዘልዬ የማመልጥበት ከአሳዳጅ ከአስጨናቂዎቼ ተሸሽጌ ምገባበት ኢየሱስ በተባለው ድንቅ ስም ነፍሴ አርፋለች ከምንም እርሱ የከፈለውን ዋጋ አልፎ ማነው እኔን ሚነካ በደም የከፈለውን ዋጋ ደፍሮ ማነው እኔን ሚጠጋ ከሳሾቼ ብዙ ናቸው ተጨባጭ መረጃ አላቸው በህጉ መሰረት ቢሄዱ አሳማኝ ነው ምክኒያታቸው በየትኛው ቅድስናዬ ልጋፈጥ ልቁም ለራሴ አንገት መድፋት መሸማቀቅ ዝምታ ብቻ እንጂ መልሴ የቤቴ ክፍተት ሳይገፋው ገፍቶ ባይገባ ከደጄ የልቤ ርቀት ሳይመልሰው ባያቅፈኝ ባይሆን ወዳጄ ሁሉን በራሱ ፈጽሞ ባያደርገኝ ኖሮ ቀና ጽድቄ ብዬ ማስቆጥረው የማሳየው ምን አለና ፍርድ አልተዛባም ልክ እኮ ነው ተከድኖ ሳይሆን ተከፍሎ ነው በከንቱ አይደለም ደስታዬ ኢየሱስ ሆኖኝ ነው ይቅርታዬ ፍርድ አልተዛባም ልክ እኮ ነው ተከድኖ ሳይሆን ተከፍሎ ነው በከንቱ አይደለም ደስታዬ ስለሆነኝ ነው ይቅርታዬ ያሸነፈልሽ ተሸነፈ ጌታሽ አበቃለት ሲሉኝ የሞተውን እንኳ ስጡኝ ያልኩበት ምክኒያት አለኝ የኔ እነደሌላው መች ሆኖ ቀርቦኝ ሲያጫውተኝ ቤዛዬ አሳ ማጥመድ ወይ በሰው ፊት ሚወራ አልነበረም ስራዬ በሀጢያተኞች ገበታ እንዴት ይቀርባል ሲሉት እኔን ከመውደዱ አልቦዘነም ከክብሩ በልጬበት ታዲያኮ አማራጭ የሌለው ሙሉ ልቡን የሰጠ ሰው ክብሩን ከመጣል ከመሸነፍ ከመውደድ ማን ሊመልሰው ፍርድ አልተዛባም ልክ እኮ ነው ተከድኖ ሳይሆን ተከፍሎ ነው በከንቱ አይደለም ደስታዬ ኢየሱስ ሆኖኝ ነው ይቅርታዬ ፍርድ አልተዛባም ልክ እኮ ነው ተከድኖ ሳይሆን ተከፍሎ ነው በከንቱ አይደለም ደስታዬ ስለሆነኝ ነው ይቅርታዬ ይቅርታዬ ይቅርታዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection