ድምፅ ነኝ እኔ የምጮሕልህ ማለት ያሰብከውን ማስተጋባልህ ይህሄው ነው ስራዬ መላክ ስትልከኝ ልጅህን ማሳየት አድርጊ እንዳልከኝ ጊዜ እና ቦታ ተገጣጥሞ ፈላጊ እና ተፈላጊ ያአንተ ማንነት ክቡርነት የኔ ማንነት ደግሞ አድናቂ ጊዜ እና ቦታው ተገናኝቶ ፈላጊ እና ተፈላጊ ያአንተ ማንነት ብርሃንነት የኔ ማንነት ደግሞ አድማቂ በተጠጋሁ ቁጥር ንፅህናህ ይበዛል መታዘዝን ፈፅመ አክሊል ተቀዳጅተሀል የእምነቴ እራስ ፈፃሚው የተሳልከው ከፊቴ እሩጫህን እንድጨርስ አንተ ላይ ነው ትኩረቴ እንደ ደመና በዙራዬ ምስክሮች እያሉ በስራ በእምነታቸው አሉ የተባሉ x2 እየሱስን ነው የማየው እየሱስን ነው ምከተለው እርሱ ነው ምሳልዬ እራሱ ነው ዋናዬ እኔ አንተን ነው የማየው እኔ አንተን ነው ምከተለው አንተ ነህ ምሳልዬ አንተ ነህ ዋናዬ ዋናዬ~~ እግሮችህ የረገጡትን በጥንቃቄ ረግጣለሁ ከፊት ከፊት ስትሄድ ከሁዕላ ከሁዕላ እከተልሃለሁx2 ባሕሪህን አጠናለሁ እንድመስልህ ቸኩላለሁ ግራ ቀኝ አላማትርም ታላቄ ነህ አይሃለሁ ባሕሪህን አጠናለሁ እንድመስልህ ቸኩላለሁ ግራ ቀኝ አላማትርም ታላቄ ነህ እሰማሃለሁ እኔ አንተን ነው የማየው እኔ አንተን ነው ምከተለው አንተ ነህ ምሳልዬ አንተ ነህ ዋናዬ ከእራሴ በላይ እርግጠኛ ነኝ በአንተ የትም ብትወስደኝ ግራ አይገባኝም ካለህ ከእራሴ በላይ እርግጠኛ ነኝ በአንተ የትም ብትወስደኝ አልጠራጠር በዛ ካለህ እኔ አንተን ነው የማየው እኔ አንተን ነው ምከተለው አንተ ነህ ምሳልዬ አንተ ነህ ዋናዬ