የአብ ትኩረት ከሆነው ከኢየሱስ በቀር የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ከልጁ በቀር የአብ ትኩረት ከሆነው ከኢየሱስ በቀር ከመንፈስ ቅዱስ ፈገግታ ከልጁ በቀር ምን መዝሙር አለን? ምን እምነት አለን? ምን ሕይወት አለን? ምን ስብከት አለን? ምን ክርስትናምን ትምህርት አለን? ከኢየሱስ ውጪ ምን እንላለን? አንተ አይደለህም ሆይ የሞታችን ከልካይ ከአባትህ ያስማማኸን የጠቡ ገላጋይ አንተ አይደለህም ሆይ የቀራንዮ ጀግና ሞትን ታሪክ ያረክ የምትመጣው ገና ኢየሱስ አይደለም ወይ የሚወድህ ልጁ መካከል የደቀክ ያረፈብህ እጁ ለሞት ያውም ለመስቀሉ የታዘዝክ ነፍስህን በፈቃድህ በምትክ ያኖርክ ታዲያ ማን በሰራው ማን ይሞገሳል? በማን ገድል ማን ይወደሳል? ወንጌል ሲባል ስሙ ሲነሳ ኢየሱስ ብቻ አብሮ ይነሳ ዘመቻ ውጡ ዘመቻ ዘመቻ እንመልስ/እናንቃ ዘመቻ ቤቱን ወደ ባለቤቱ መድረኩን ወደሚያምርበቱ ዘመቻ አንቺ ውርንጭላ ንጉስሽን አስቀምጪ ሲቀመጥብሽ ነው ዘንባባ ምትረግጪ አንቺው ሙሽሪት ዝርግፍ ጌጥሽን አንሺ ከሴቶች መካከል ሞገስ ልዩነትሽን አንቺ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን መልሺ መጥቶ ሚወስድሽን ውቡን ሙሽራሽን ጊዜው ምን ባይመስል ግራ ቢገባሽም የእረኞች አለቃ ያንኳኳል ደጅሽን እንዴት ቤቱ ፈርሶ የእኛ ቤት ያምራል? እርሱ ተረስቶ የእኛ ይሰራል? ዳስ በሙሉ፣ ዙፋናት ሁሉ ለአንድያው ልጅ ለእርሱ ይገባል ዘመቻ ውጡ ዘመቻ ዘመቻ እንመልስ/እናንቃ ዘመቻ ቤቱን ወደ ባለቤቱ መድረኩን ወደሚያምርበቱ ዘመቻ ትውልድ አለ ኢየሱስን እንደጧፍ የሚያበራ የአምላኩን ሕግ የሚያውቅ አልፎም የሚፈራ ለወርቁ ምስል እንዳይሰግድ አምላኩ የሆነለት ወርቅ የሚያብለጨልጭ ጌጥ እንዳይሰጋ የእቶኑን ጉልበት እግዜሩን የሚያውቀው እንደሚባላ እሳት ክርስትናን ከቁስ ሳይሆን ከጌታ የጀመረ እውነተኛ ባሪያ ለጌታው ያደረ ዓለማዊነትን እየቀለበ ማያፋፋ የመንፈሱ ወዳጅ ከቃሉ የተሰፋ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር የሚገለጥ በሕይወት በመኖር አንተ ሲባል የሚል እሱ፥ ጥቅሙን መብቱን የሚተው ለእሱ ትኩረት ሁሉ ወደ ኢየሱስ፣ ወደ ኢየሱስ አይኖች ሁሉ ወደ ኢየሱስ፣ ወደ ኢየሱስ