የማለዋውጠው እውነት ነው በሁኔታዎች የማላጥፈው የሚመሰክረው ህይወቴ መልካምነትህን ነው አባቴ የሚዘምረው አንደበቴ መልካምነትህን ነው አባቴ ኢየሱስ መልካም ልበልህ (መልካም ነህ) እንዲህ ነው እኔ የማውቅህ (መልካም ነህ) መመስከር ነው የኔ ስራ (መልካም ነህ) መንገድን እንደምትመራ (መልካም ነህ) መልካም ነህ (*4) ከራስህ ከማንነትህ (መልካም ነህ) በጎ ነው ሁሌም አላማህ (መልካም ነህ) ፈተናዬን ታግዛለህ (መልካም ነህ) በዛም ውስጥ ድል ትሰጣለህ (መልካም ነህ) መልካም ነህ (*4) ላይገባኝ ይችላል እጅግ ብዙ ነገር እንዲህ እንዲያ ብዬ በእርግጥ ለመናገር ግን አንዱ ሁልጊዜም ለማለት ምደፍረው ማልሸሸው እውነትህ መልካምነትህ ነው (ማልክደው እውነትህ መልካምነትህ ነው) (ማወራው እውነትህ መልካምነትህ ነው) መልካም ነህ (*4)