Song Lyrics

መድሃኒቴ

Fenan Befkadu
Special Edition
ገና በማለዳ ብርሃን ሳይፈነጥቅ ጨረቃም ቦይታዋን ለፀሃይ ሳትለቅ አይኖቼ ተከፍተው ከእንቅልፌ ስነቃ ኢየሱስን እሻለው ኢየሱስን ጠራለው ሌሊቱ ሲነጋ ሲነጋ ሲነጋ ኢየሱስን ልጠጋ*2 ሲነጋ ሲነጋ ወደ እየሱሴ ጋ በቀትር ምሳ ሰዓት ድካም ሲመጣብኝ ልቤ እረፍት ሲሻ ዝለት ሲጫጫነኝ ከቶ ማልዘነጋው የነፍሴ ረሃቧ ኢየሱስን እሻለው ኢየሱስን ጠራለው ጥጋቤ ነውና ! በቀትር በቀትር ኢየሱስ ላናግር በቀትር ከእሱ ጋር ልማከር *2 በቀትር ማታ አመሻሽ ላይ አይኔ ባይከደን ፀሃይም ስትሸሽ ድካም ሲሰለጥን ሰውነት ሲያቅተው መቋቋም እንቅልፍን መተኛት አልሻም ቀኑም አይዘጋም ሳልጠራው ስምህን! በምሽት በምሽት ኢየሱስን ልጥራበት በምሽት ከሱጋ ልጫወት በምሽት በምሽት ለነፍሴ ላስታዉሳት በምሽት መድሃኒቴ ስምህ ጠራለው*2 ጌታ ኢየሱስ ስምህን ጠራለሁ ቀርበህ ሳለህ ስምህ ጠራለው የኔ አፀናኝ ስምህ ጠራለው መድሃኒቴ ስምካ ክፅውህዬ*2 ጎይታ ኢየሱስ ስምካ ክፅውህዬ ፈይሳኮ መቃኬን ዋማ ጎፍታ ኢየሱስ መቃኬን ዋማ ጋር ጋራ ኮ መቃኬን ዋማ መድሃኒቴ ስምህን ጠራለው የኔ አፀናኝ ስምህን ጠራለው መዳኛዬ ስምህን ጠራለው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection