አዝ፦ አንተን ካገኘሁ ጀምሮ ሕይወቴ በአንተ አምሮ የፍቅርህን ብዛት አልችልም ልገልጻት የምህረትህን ብዛት አልችልም ልገልጻት (2x) የፈሰሰው ሠማያዊ ፀጋ አኑሮኛል ከአንተ ጋ የመረጥከኝ ተባረክልኝ የወደድከኝ ተባረክልኝ በመስቀል ላይ ስለ እኔ ሞተሃል አበሳዬን ወስደሃል ምን ልክፈልህ እንዲያው ልገዛልህ (2x) ሰው ያረገኝ ፀጋህ ነው ታሪኬን ለውጦ ከሞት አስመልጦ ጌታ ሆይ ተመስገን (2x) አዝ፦ አንተን ካገኘሁ ጀምሮ ሕይወቴ በአንተ አምሮ የፍቅርህን ብዛት አልችልም ልገልጻት የምህረትህን ብዛት አልችልም ልገልጻት (2x) የዓለም ክብር ሃብት አያጓጓኝም ከአንተ አይበልጥብኝም መርጬሃለሁ እከተልሃለሁ የምህረትህ የፍቅርህ ብዛቱ አልበረደም ግለቱ ያዘምረኛል ተድላዬ ሆኖኛል ያዘምረኛል ሞገሴ ሆኖኛል ሰው ያረገኝ ፀጋህ ነው ታሪኬን ለውጦ ከሞት አስመልጦ ጌታ ሆይ ተመስገን (2x) አዝ፦ አንተን ካገኘሁ ጀምሮ ሕይወቴ በአንተ አምሮ የፍቅርህን ብዛት አልችልም ልገልጻት የምህረትህን ብዛት አልችልም ልገልጻት በመረቅህልኝ አዲስ ህያው መንገድ ደስ እያለኝ ልራመድ መጨረሻዬ ኢየሱስ ጌታዬ መጨረሻዬ አንተ ነህ ጌታዬ የሩቅ አገር የፅዮን ተጓዥ ነን በሠማይ አገር ያለኝ ታድያለሁ አገሬ ገባለሁ ታድያለሁ ዘለዓለም አርፋለሁ ሃሌሉያ ሰው ያረገኝ ፀጋህ ነው ታሪኬን ለውጦ ከሞት አስመልጦ ጌታ ሆይ ተመስገን (2x)