Song Lyrics

አንተን አንተን አለች

Agegnehu Yideg
Bizu Yehonkilign
በእንባ አንተኑ ደጅ ልጥና በልጅህ አትጨክንምና በእንባ አባቴን ደጅ ልጥና ሌላ የለኝምና (2x) አትጨክንምና ሌላ የለኝምና (2x) ከምድረ በዳው ኑሮ ከዛ ከቃጠሎ አንተ ነህ የታደካት ደርሰህላት ቶሎ ስለዚህም ነፍሴ አንተን አንተን አለች ቀንና ሌሊት ፊትህን ፈለገች አዝ፦ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (4x) ኢየሱስ አንተ ነህ ለነፍሴ ትርጉሟ እውነተኛ ወዳጅ የኑሮ ጣዕሟ ያለ አንተ መኖር አይሆንላትም መጠጊያ ጐጆ ሌላ የላትም አዝ፦ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (4x) ባስለመድከኝ ስፍራ እጠብቅሃለሁ አንተን ካላገኘሁ መቼ እተኛለሁ ሌሊቱ ጭር ብሏል ሰው ሁሉ ተኝቷል ከአንተ ጋር መሆኑ ነፍሴ ግን አምሯታል አዝ፦ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (4x) እግዚአብሔር አለቴ እመካብሃለሁ እስከ ዘለዓለሙ ተስፋ አደርግሃልሁ ምንም ሳትሰራልህ ነፍሴን ወደሃታል ለቀሪውስ ጉዞ ምንድን ያሰጋታል በእንባ አንተኑ ደጅ ልጥና በልጅህ አትጨክንምና በእንባ አባቴን ደጅ ልጥና ሌላ የለኝምና (2x) አትጨክንምና ሌላ የለኝምና (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection