Song Lyrics

ምን እሆናለሁ

Agegnehu Yideg
Bizu Yehonkilign
ምድር ስትጨነቅ ዘመኑ ሲከፋ እኔ አንተን ይዣለሁ የዘለዓለም ተስፋ በቤትህ አለሁኝ እስካሁን ተጉዤ እየዘማመርኩኝ በገናዬን ይዤ አዝ፦ ምን እሆናለሁ ጌታ ምን እሆናለሁ ምን እሆናለሁ አንተን አግኝቻለሁ ምን እሆናለሁ በቃ ምን እሆናለሁ ምን እሆናለሁ ተደግፌሃለሁ (5x) ስለዚህ አመልክሃለሁ (2x) በቤትህ ምን አጥቻለሁ ገና እኖራለሁ ማረፊያ አንተ ነህ (3x) ተጠለልኩ በጥላህ ማረፊያ አንተ ነህ (3x) ተመካሁ በሥምህ ምን ይዋጠኝ ለኑሮዬ አልሰጋም የጐደለኝ የለም አንተን ከተጠጋሁ በሰላም ወጥቼ በሰላም ገባለሁ ዓለም የሌላትን ሰላም አግኝቻለሁ አዝ፦ ምን እሆናለሁ ጌታ ምን እሆናለሁ ምን እሆናለሁ አንተን አግኝቻለሁ ምን እሆናለሁ በቃ ምን እሆናለሁ ምን እሆናለሁ ተደግፌሃለሁ (5x) ስለዚህ አመልክሃለሁ (2x) በቤትህ ምን አጥቻለሁ ገና እኖራለሁ ማረፊያ አንተ ነህ (3x) ተመካሁ በሥምህ የዚህ ዓለም ሰዎች በሚያልፈው ሲመኩ የሰውን ማንነት በገንዘብ ሲለኩ እኔ ግን በአንተ ልመካ በማታልፈው ጌታ ስለምታዋጣኝ የማታ ማታ አዝ፦ ምን እሆናለሁ ጌታ ምን እሆናለሁ ምን እሆናለሁ አንተን አግኝቻለሁ ምን እሆናለሁ በቃ ምን እሆናለሁ ምን እሆናለሁ ተደግፌሃለሁ (5x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection