Song Lyrics

የኤማሁስ መንገደኞች

Agegnehu Yideg
Hayilegna Endante Yelem
የተስፋን ቃል የሰጣችሁ የታመነ ነውና በስፍራችሁ ሆናችሁ ጠብቁት ታገሱና እግዚአብሔር አይጨክንም ያስብላችኋል እርሱ ሰብሯችኋልና እርሱ ይጠግናችኋል አዝ፦ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ጠውልጋችሁ ዝላችኋል የምትሉትን አታውቁም ስንፍናና ዝንጉነትን ለምን ከእናንተ አታርቁም እግዚአብሔር እረስቶናል እባካችሁን አትበሉ የሚበዣችሁ ኢየሱስ ታማኝ ነው እኮ ለቃሉ አዝ፦ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ይቤዠናል ብለን ነበረ ተስፋ ያደረግነው ለካስ የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደዚህ ዓይነት አምላክ ነው ስለምን እንደዚህ ትናገራላችሁ ጌታችን ከሞት ተነስቶ አሁን እኮ አለ አብሯችሁ አዝ፦ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ስፍራችሁን ለቃችኋል እግዚአብሔር ያላችሁን በሙሉ ዘንግታችኋል የገባላችሁን ተስፋ እናንተ እንኳን ብትረሱ እግዚአብሔር ግን አይረሳም ከሞት ተነስቷል ንጉሡ አዝ፦ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection