ትላንት በእሳቱ ላይ ተራመድን ፡ በእግዚአብሔር ፀጋ ሁሉን አለፍን ፡ ማእበል ወጅቡን ፡የገሰፀው ፡ የያዕቆብ አምላክ ከእኛ ጋር ነው የነሙሴ አባት ከእኛ ጋር ነው ፡ ከክብር ወደ ክብር እንሻገራለን ፡ ኢየሱስን ይዘን ማነው ሚቋቋመን ፡ ገና እናብባለን! ደረቁ ስንባል ለመለምን በእግዚአብሔር ታደሰ ኃይላችን ገና በምድር ሁሉ እንበዛለን ወንጌሉን በስልጣን እንሰብካለን ከክብር ወደ ክብር እንሻገራለን ፡ ኢየሱስን ይዘን ማነው ሚቋቋመን ፡ ገና እናብባለን!