ከባርነት አገር ወደ አንተ ያመጣኸን ቀንበርን ሰባብረህ አርነት ያወጣኸን በጨለማ ያለ ህዝብ ታላቅ ብርሃን አየ ከሰቆቃ ኑሮ ከሰይጣን ተለየ አዝ፦ ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ እግዚአብሔር ኃያል ነህ ማንንም አትንቅም የሚጤሰውን ጧፍ አጥፍተህ አታውቅም ለደካማው ኃይልን ለጭንጋፉ ሞገስ ከፍ በል ጌታዬ ለዘለዓለም ንገሥ አዝ፦ ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሁሉ ማኅተሙን ሊፈቱ ማናቸውም አልቻሉ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ አንተ ግን ችለሃል ማኅተሙን ልትፈታ አዝ፦ ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ ሞተሃል ተብሎ እኛም ተስፋ ቆርጠን በራችንን ዘግተን አዝነን ተቀምጠን አንተ ግን ልዩ ነህ ታሪክ ገልብጠሃል ሞትና መውጊያውን ለዘለዓለም ሰብረሃል አዝ፦ ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ ትዕቢተኛውን ፈርዖን ሊያጠፋን ሲነሳ ዙሪያችንን ሲዞር ሊውጠን እንደ አንበሳ ቀድመህ ደረስክና አፉን ለጐምክልን ምን እንበላ ሌላ ለእኛስ ዘለዓለም ንገሥልን አዝ፦ ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ