Song Lyrics

የመጨረሻዬ

Agegnehu Yideg
Haleluya Talak Neh
ዓለም ስትንጫጫ ወከባ ሲበዛ ለእኔ ግን አንተው ነህ የዘለዓለም ቤዛ መሸሸጊያየ ነህ ይሄው አስከዛሬ አሁንም አደራ አድርሰኝ አገሬ (መደምደሚያየ ነህ የመጨረሻዬ ኢየሱሴ ለእኔ ለእኔ እየሱሴ ለኔ) (2x) ሰው ሁሉ ይሄዳል ወደየ አምላኩ ስዓቱ ሲያበቃ የዚች ዓለም ልኩ ለእኔ ግን አንተው ነህ ለነፍሴ ውስኔ ከኃጢአት ያዳንከኝ ኢየሱስ መድህኔ አዝ መደምደሚያየ ነህ በጓዳዬ ያለህ አልማዜ ንብረቴ ለሰው የማሳይህ ትምህክቴ ኩራቴ እውነተኛ ወዳጅ ቀን የማይለውጥህ አነሰብኝ እኔስ እድሜዬን ብሰጥህ አዝ መደምደሚያየ ነህ እየመሸ ሄደ ፀሐይ ዘቀዘቀች ነፍሴ ግን አሁንም አንተን አለወጠች የዚህ ዓለም ክብር ሃብት ብልጽግና ከአንተ ዓይነጥሏትም ትኖራለች ገና አዝ መደምደሚያየ ነህ 11 ተራ ቁጥር ያልተዘጋጀለት ተስፋችን ዛሬም ጌታ ነው አይለወጥም በዙፋኑ ላይ ዓይናወጥም አሜን እግሩ ስር ሆነን (እናመስግነው) (2x) ለእኛ ያረገው እጅግ (ብዙ ነው)፪ ጠላቴም አስቦኝ ጉድጓዱን ደፍኖ ስንት ጊዜ አሻገረኝ ጌታ ድልድይ ሆኖ በፊታችን ሆኖ እየተዋጋልን በላይ የቆመትን ወደታች ጣለልን አዝ ተስፋችን አላማ ይዞ የሚያስፈራ በአንተ ያመለጠ ከታላቅ መከራ የሰይጣንን ምሽግ ደርምሶ ያለፈ የአንተ ህዝብ ይኖራል ሁሌ እንዳሸነፈ አዝ ተስፋችን የአምላኩ ክብር በፊቱ ያበራል ተራራ ላይ ቆሞ መዝሙር ይዘምራል ሞገስ ተፈራርተን አድርገንበታል ቀናቶች ሳይቀሩተገዝተውለታል አዝ ተስፋችን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection