አንተ አገልጋይ ጌታን የምትወደው በድካም ሕይወት ያለኸው ከሸለቆ ውጣ ና ና ዛሬም ኢየሱስ(ጌታ) ይወድሃልና ይጠራሃልና እርሻውን አርሰህ ጐልጉለህለመከሩ ደክመህ ስለወንጌል ብለህ ብዙ ዋጋ ከፍለህ (አሁን ምነው ደከምህ አዝመራው ሲቃረብ የዚች ዓለም አንድ ቀን አያልቅም ) (2x) አዝ አንተ አገልጋይ ተስፋ አይቆረጥ በጌታ ምህረቱ ብዙ ዓለም አድክማቸው የደነዘዙ (የደከመን ጉልበት እንደ ንስር ያድሳል ወደ ቀደመውክብር ዳግም ይመልሳል) (2x) አዝ አንተ አገልጋይ ዘመኑ ሲቃረብ ክፉንም ዙሪያህ ሰው የላዩን ትቶ የምድሩን ያስባል (ነገር ግን ሁሉ ከንቱ ነው ንፋስን መከተል የከበረውብድራት ኢየሱስን ማገልገል) (2x) አዝ አንተ አገልጋይ ወንድሜ ሆይ ስለምን ተስፋ ቆረጥክ ጌታ እኮ ይወድሃል ያውም እስከ መስቀል ሞት ዛሬ ና ተነስ ጌታ ሳይመጣ አገልግለው አንተ መስክረህላቸው ያስተማርካቸው ዛሬ አድገው ቤቱ አገልጋዮች ናቸው (ዘወትር በጌታ ፊት ይጸልዩልሃል እግዚአብሔርም ታማኝ ነው አንተን ያስብሃል) (2x) እግዚአብሔር እንደ ሳምሶን አንዴ ያስብሃል