(፮ኛው መዝመር ተቀያይሯል ከ (፯ኛው ጋር እናንተ መኳንት በሮችን ክፈቱ የዘለዓለም ደጆች ይከፈቱ (የክብር ንጉሥ ይግባ) (3x) ኢየሱስ ጌታ ይግባ ፊተኛ ኋለኛ አልፋና ኦሜጋ ነው ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለው ነገሥታትን ሁሉ ብቻውን ያሸነፈ ህዝቡን ከሞት ያተረፈ (እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል እግዚአብሔር ነው በሰልፍ ሃያል እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል) (2x) አዝ እናንት መኳንት በአምላካችን ፈት በኃይሉ ማን ይቆማል ነጐድጓድ ድምጹን ማን ይሰማል ተራራን በግርማው እንደሰም ያቀለጠው ምድረ በዳውን ያናወጠው (እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል እግዚአብሔር ነው በሰልፍ ሃያል እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል) (2x) አዝ እናንት መኳንት እግዚአብሔር ተዋጊ ስሙም ደግሞ እግዚአብሔር ነው የሰይጣንን ሰልፍ የበተነው ኃይሉ እጅግ ታላቅ ነው በደመናት ላይ ይራመዳል ትቢተኞችን ያዋርዳል (እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል እግዚአብሔር ነው በሰልፍ ሃያል እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኋያል) (2x) አዝ እናንት መኳንት ክብሩን ሊያሳዬን ሥጋ ለብሶ የተገለጠው ከአርያም ቃሉን የሰጠው በሞቱ ሞታችንን ለዘለዓለሙ የገደለው አውሬውን ወደሳት የጣለው (እግዚአብሔር(ኢየሱስ) ነው ብርቱና ኋያል እግዚአብሔር(ኢየሱስ) ነው በሰልፍ ሃያል እግዚአብሔር(ኢየሱስ) ነው ብርቱና ኋያል) (2x) አዝ እናንት መኳንት