ምሥጋና አምልኮ ይዤ መጣሁ አንተን የሚመስል አጣሁ ተወደስ ተቀደስ ለዘለዓለም የሚወዳደር የለም (አንተን የሚመስል የለም) (4x) የፀሐይ ድምቀትዋ የምድር ስፋቷ የውቂያኖስ ጥልቀት የሰማይ ርቀት አንተ ባለግርማ ከማን ላወዳድርህ ወጥቸ ወርጀ አጣሁ የሚመስልህ ክረምት አለፈ በጋው መጣ አንዱ ወረደ ሌላው ወጣ ግን እስከዛሬ ሕያው የሆነው የእኛውኢየሱስ ብቻ ነው (አማኑኤል ብቻ ነው) (2x) የእኛጌታ ብቻ ነው የእኛኢየሱስ ብቻ ነው አዝ ምሥጋና አምልኮ የነፋስ ሽውታ የእጽዋት ሽታ የወንዝ የጅረቱ የአእዋፍ የአራዊቱ አድንቄአድንቄ ሁሉን በየተራ መጨረስ አልቻልኩም ጌታ የአንተን ስራ ክረምት አለፈ በጋው መጣ አንዱ ወረደ ሌላው ወጣ ግን እስከዛሬ ሕያው የሆነው የእኛውኢየሱስ ብቻ ነው (አማኑኤል ብቻ ነው) (2x) የእኛጌታ ብቻ ነው የእኛኢየሱስ ብቻ ነው አዝ ምሥጋና አምልኮ የሰው ልጆች ውበትየጀግኖቹ ጉልበት የባለጸጋው ፍርድ የጠቢባን ጥበብ ከማን ላወዳድረው ጌታ የአንተን ዝና በዘመናት ሁሉ ብቻህን ገናና ክረምት አለፈ በጋው መጣ አንዱ ወረደ ሌላው ወጣ ግን እስከዛሬ ሕያው የሆነው የእኛውኢየሱስ ብቻ ነው (አማኑኤል ብቻ ነው) (2x) የእኛጌታ ብቻ ነው የእኛኢየሱስ ብቻ ነው አዝ ምሥጋን አምልኮ ቅኔው ማህሌቱ የሙዚቃው ስልቱ ስዕሉም ተኩሎ ማን አንተን አክሎ ቃላት አይገልጹህም ታላቅነትህን በገባን መጠን እናክብር ስምህን ክረምት አለፈ በጋው መጣ አንዱ ወረደ ሌላው ወጣ ግን እስከዛሬ ሕያው የሆነው የእኛውኢየሱስ ብቻ ነው (አማኑኤል ብቻ ነው) (2x) የእኛጌታ ብቻ ነው የእኛኢየሱስ ብቻ ነው