ወይን አብቦ አፈራ በለስ መልሶ ጐመራ የዜማ ጊዜ ደረሰ አምላኬ/እግዚአብሔር ኃይሌን አደሰ (2x) አዝ፦ ጠላት ስማ እፈር እፈር ሰይጣን ስማ እፈር እፈር ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር (2x) ሁሌ እየዞርክ ዙሪያዬን ስታጣጥለው ተስፋዬን የታመንኩት ወዳጅ ደረሰና አንደበቴን ሞላው በምሥጋና የታመንኩት ኢየሱስ ደረሰና እኔንም አቆመኝ እንደገና አዝ፦ ጠላት ስማ እፈር እፈር ሰይጣን ስማ እፈር እፈር ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር (2x) ነፍስ ዘራ የሞተ ከጉድጓድ የተከተተ የሰማይ ደጆች ተከፈቱ ለቤቴ በዛ ተዓምራቱ (2x) አዝ፦ ጠላት ስማ እፈር እፈር ሰይጣን ስማ እፈር እፈር ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር (2x) ጌታን የሚጠባበቁ ይከብራሉ እንጂ አይወድቁ ኃይላቸውንም ያድሳሉ የጠላትን ደጅ ይወርሳሉ (2x) አዝ፦ ጠላት ስማ እፈር እፈር ሰይጣን ስማ እፈር እፈር ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር ከፊቱ አልጣለኝም እግዚአብሔር (2x)