Song Lyrics

ለምን እፈራለሁ

Agegnehu Yideg
Chelema Bera
አዝ፦ እግዚአብሔር እያለ ለምን/እንዴት እፈራለሁ አምና ነው ካቻ አምና ነው ሁሉን አይቻለሁ አምና ነው ካቻ አምና ነው ክንዱን አይቻለሁ ( 2x) ሸለቆ ተራራው ከፍታው ዝቅታው አቤት ከእርሱ ጋራ ከፊት ከፊት ሲሄድ እጄን ይዞ እኔን እየመራ አዎ አይቻለሁኝ ጥበቃውን ምህረቱን ለልጁ እንዳበዛ ዛሬም ቢሆን አምነዋለሁ አይተወኝም እንዲሁ እንደ ዋዛ አዝ፦ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምና ነው ካቻ አምና ነው ክንዱን አይቻለሁ ( 2x) ከእናቱ ቤት ከአባቱ ከዘመዱ አብርሃምን ብቻውን ጠራና እኔ ወደ ማሳይህ አገር ሂድ ብሎ አዘዘና አዎ ቃልኪዳን ገባለት ሊባርከው ለዘሩ ምድርን ሊያወርሰው እንደ ተናገርው የብዙ አባት አደረገው አዝ፦ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምና ነው ካቻ አምና ነው ክንዱን አይቻለሁ ( 2x) በቃሉ ተናግሮኝ ጠብቄው በፀሎቴ ምንም አልነሳኝም አባት አለኝ ብዬ ተመክቼ አላሳፈረኝም አዎ በፍፁም አልሰጋም ትደላደልኩ በአባቴ ቤት እግሬ ተተከለ ነገም ለሚሆነው አልፈራም አማኑኤል አለ አዝ፦ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምና ነው ካቻ አምና ነው ክንዱን አይቻለሁ አምና ነው ካቻ አምና ነው ክንዱን አይቻለሁ ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection