በግብፃውያን መንደር ጨለማው በርክቷል በእኔ ቤት ብርሃኔ ኢየሱሴ በርቷል የጠላቴን መንገድ ሁካታ ሞልቶታል የእኔ ግን ድንኳኔ በዕልልታ ተሞልቷል አዝ፦ ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (፬x) ሲሳካም ዕልልታ ሳይሆንም ዕልልታ ኢየሱስ ነው ጌታ ተራራም ዕልልታ ሸለቆም ዕልልታ አቀዋለሁ ጌታ አዝ፦ ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (፬x) እያልኩኝ ብውል ባድር አይገልጥም የአንተን ክብር እያልኩኝ በበገናዬ ማደሪያህ ልግባ ጌታዬ አዝ፦ ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (፬x) ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ሆነው የመጣህላቸው ሲዘምሩ ነው የውህኒው መሠረት የተናወጠው ሲቆዝሙ አይደለም በዕልልታ እኮ ነው አዝ፦ ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (፬x) ከሁኔታ በላይ የሚያዘምረኝ ተቆጥሮ የማያልቅ ውለታ አለብኝ ኦ ዘሬ ቢገዛለት ፍጥረትም ቢያመልከው የእርሱን ህልውና ማነው የሚተርከው በበጋም ዕልልታ በክረምት ዕልልታ አትለወጥ ጌታ ሲዘጋም ዕልልታ ሲከፈት ዕልልታ አንተ ብቻ ጌታ አዝ፦ ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (፬x) እያልኩኝ ብውል ባድር አይገልጥም የአንተን ክብር እያልኩኝ በበገናዬ ማደሪያህ ልግባ ጌታዬ አዝ፦ ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (፬x) ግርማውና ክብሩ ፊቱ ይታየኛል ነፍስም አልቀረልኝ ዕልልታ ሞልቶኛል (እሰይ የእኔ ጌታ) ከበሮ ይመታ ይደርደር በገና ከጥንት ለዘለዓለም ብቻውን ገናና አዝ፦ ዕልልታ ለአንተ ይሁን ጌታ (፲ 2x)