Song Lyrics

የኤማሁስ መንገደኞች

Agegnehu Yideg
Bizu Yehonkilign
የተስፋን ቃል የሰጣችሁ የታመነ ነውና በስፍራችሁ ሆናችሁ ጠብቁት ታገሱና እግዚአብሔር አይጨክንም ያስብላችኋል እርሱ ሰብሯችኋልና እርሱ ይጠግናችኋል አዝ፦ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ጠውልጋችሁ ዝላችኋል የምትሉን አታውቁም ስንፍናና ዝንጉነትን ለምን ከእናንተ አታርቁም እግዚአብሔር ረስቶናል እባካችሁን አትበሉ የሚበዣችሁ ኢየሱስ ታማኝ ነው እኮ ለቃሉ አዝ፦ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ይቤዠናል ብለን ነበረ ተስፋ ያደረግነው ለካስ የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደዚህ አይነት አምላክ ነው ስለምን እንደዚህ ትናገራላችሁ ጌታችን ከሞት ተነስቶ አሁን እኮ አለ አብሯችሁ አዝ፦ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ስፍራችሁን ለቃችኋል እግዚአብሔር ያላችሁን በሙሉ ዘንግታችኋል የገባላችሁን ተስፋ እናንተ እንኳን ብትረሱ እግዚአብሔር ግን አይረሳም ከሞት ተነስቷል ንጉሡ አዝ፦ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection