ተክሎ መሄድ የአንተን ፍለጋ ምነኛ መልካም ነው ቢበዛልኝ ፀጋ አስከብሬህ ልለፍ እንደ አባቶቼ ዓለም እና ትርፏን ሁሉን ንቄ ትቼ (2x) አዝ፦ ክርስትናን መኖር ዋጋ በመክፈል ነው ግን የለብስኩት ሥጋ እጅግ ደካማ ነው ከጐኔ በመቆም ካላበረታኸኝ ታውቃለህ ጌታ ሆይ እኔ ደካማ ነኝ (2x) ዘወትር በፀሎት በፊትህ ልደፋ በውስጤ ያኖርከው እሳቱ እንዳይጠፋ ገና ላገልግልህ በኃይል ተሞልቼ ጉብዝናዬን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼ (2x) አዝ፦ ክርስትናን መኖር ዋጋ በመክፈል ነው ግን የለብስኩት ሥጋ እጅግ ደካማ ነው ከጐኔ በመቆም ካላበረታኸኝ ታውቃለህ ጌታ ሆይ እኔ ደካማ ነኝ (2x) ባላደራነቴን ችላ እንዳልለው የወንጌልን ዕንቁ ለራ እንዳልጥለው ታማኝ አድርገህ ቆጥረህ በቤትህ የሾምከኝ ከፈተናዎቼ ፀጋህ ያሾልከኝ/ያስመልጠኝ (2x) ሰርክ እናይሳነኝ መንጋህን በመገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ የከበረ መዝገብ ያስቀመጥክ አንተ ነህ እንደ ኃይልህ ብዛት እስከ መጨረሻው ሕይወቴን አግዛት (2x) አዝ፦ ክርስትናን መኖር ዋጋ በመክፈል ነው ግን የለብስኩት ሥጋ እጅግ ደካማ ነው ከጐኔ በመቆም ካላበረታኸኝ ታውቃለህ ጌታ ሆይ እኔ ደካማ ነኝ (2x)