የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ ሁልጊዜ አመልክሃለሁ ደግሜ ደግሜ ባነሳህ እኔስ መች ጠግባለሁ የነፍሴ ንጉሥ ነህ አንተ የሕይወቴ መሪ የፍጥረት አብ ጌታ ለዘለዓለም ነዋሪ አዝ፦ እኔ እገረማለሁ (3x) ፊትህን እያየሁ እኔስ እደነቃለሁ (3x) ማዳኑን እያየሁ ሃሌሉ ሃሌሉያ ልዘምር ልዘምር ሥምህን ላክብር ልዘምር ልዘምር ጌታዬ ላክብር በገናን ልደርድር በፊትህ ሥምህን ልቀድስ ጣቶቼን ዘመቻ ያስተማርካቸው አንተ ነህ ኢየሱስ በክብር ላይ ክብር ይጨመርልህ በሰማይ በምድር አንተን አጣ የሚመስልህ አዝ፦ እኔ እገረማለሁ (3x) ፊትህን እያየሁ እኔስ እደነቃለሁ (3x) ማዳኑን እያየሁ ሃሌሉ ሃሌሉ-ያ ልዘምር ልዘምር ሥምህን ላክብር ልዘምር ልዘምር ጌታዬ ላክብር በነጋ በጠባ ከውስጤ ምሥጋና ይፈልቃል ያረክልኝ ተነግሮ ተዘምሮ መች ያልቃል አንተ ነህ እንጂ ለእኔ ክብሬ ሌላ ክብር የለኝ ከኃጢአት አጥበህ ቀድሰህ ሥም ያወጣህልኝ