Song Lyrics

ወዳጅ ማን አለ

Nahom Markos
Ewunetegna Selam
የማይከዳ ትቶ የማይሄድ ሃብት ንብረት ፊት አይቶ የማይወድ እውነተኛ ወዳጅ ማን አለ እንደ ኢየሱስ ያለ (2x) ታናሽነቴን ያልናቀ እጁን ዘርግቶ ጠራኝ እወድሃለሁኝ ልጄ አንተ የእኔ ነህ አለኝ በስደት በባርነት አገር ታሪኬን በክብር ቀየረ ብቻዬን ነኝ ባልኩበት ጊዜ ለካ ጌታ አብሮኝ ነበረ (2x) (አይቻለሁ) ወዳጅ መስሎ ስንቱ ቀርቦኝ (አይቻለሁ) ምድረ በዳ ሲሄድ ጥሎኝ (አይቻለሁ) አንተ ግን ጌታ ስቲዘኝ (አይቻለሁ) በድካሜ እንኳን ተሸከምከኝ አይለወጥ ፍቅርህ አይሰለች ትክሻህ የሚያልፈው ሁሉ ሲጸየፈኝ ቁስሌን ጠራርገህ አነሳኸኝ አይለወጥ ፍቅርህ አይሰለች ትክሻህ የሚያልፈው ሁሉ ሲጸየፈኝ አባት አንተ ነህ የተጠጋኸኝ (አይለወጥ ፍቅርህ (3x)) (አይሰለች ትክሻህ) ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ወዳጄ እኔስ አላየሁም እንደ ኢየሱስ የሚመች ሁሉም በሸሸበት በዚያ በከባዱ ጊዜ ኢየሱስ አይደለም ዎይ ያወጣኝ ከሃዘን ከትካዜ (2x) አቤት የአንተስ ፍቅር አቤት ቸርነትህ ለጠላትስ አይቀር በመስቀል መሞትህ ልቤ አቅም አጣ በፍቅርህ ጉልበት ተሸነፍኩኝ በቃ ገዛኝ ማንነትህ (2x) ማን ብዬ እጠራሃለሁ ፍቅርህ ከምለው በላይ ነው ኢየሱሴ ትለያለህ እንደ አንተ ያለ ማን ወዳጅ አለ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection