እውነተኛ ሰላም እውነተኛ ደስታ የገባኝ አሁን ነው አንተን ስይዝ ጌታ ብዙ ተቅበዘበዝኩ ደህንነት ፍለጋ በማመኔ ብቻ ላገኘው አንተ ጋ ምቾቴ አንተ ነህ ሰላሜ አንተ ነህ እረፍቴ አንተ ነህ ልቤ ያረፈብህ (2x) ልቤ ያረፈብህ (4x) (ያረፈብህ (8x)) ወርቅ ዕንቁ ቢሞላ ላይሰጠኝ ሰላም ዕውቀት ቢደረደር አያሳርፍም ነፍሴ ስትጨነቅ ጥያቄዋ በዝቶ መመለስ የሚችል ከወዴት ተገኝቶ አንተ ስትገባ ወደ ሕይወቴ ተለዋወጠ ማንነቴ ጥያቄ ሁሉ ተመለሰ ሰላም ደስታ በውስጤ ፈሰሰ (2x) በለስ ባታበቅል ፍሬዋ ባይገኝ ምድራዊ ነገሬ ቢጨላልምብኝ ቢጐድል ቢሞላ እኔ አልገረምም በዚህ ሁሉ መሃል ሰላሜ አይጐልም የማዳኑን ክንድ አልብሶኛል መጐናጸፊያን ደርቦልኛል በአምላኬ ሃሴት አደርጋለሁ ለዘለዓለም በደስታ ኖራለሁ (2x) እውነተኛ ሰላም እውነተኛ ደስታ የገባኝ አሁን ነው አንተን ስይዝ ጌታ ብዙ ተቅበዘበዝኩ ደህንነት ፍለጋ በማመኔ ብቻ ላገኘው አንተ ጋ ምቾቴ አንተ ነህ ሰላሜ አንተ ነህ እረፍቴ አንተ ነህ ልቤ ያረፈብህ (2x) ልቤ ያረፈብህ (4x) የሚያውቁኝ በሙሉ እጅግ ተገረሙ እንዲህ የሚያሳርፍ ምን አገኘ? እያሉ ፍፁም መረጋጋት እርፍ ማለት የትም አይገኝም በሌለህበት ሁሉን ነገር ለአንተ ሰጥቼህ ተደላደልኩኝ አረፍኩብህ የማይለወጥ ፍቅርህ ሲነካኝ ሌላው ሁሉ ከንቱ ሆነብኝ (2x) የደስታዬ ምንጭ ኢየሱስ ሰላም የሆነኝ ኢየሱስ ማንም ከእንግዲህ ኢየሱስ የማይለያየኝ ኢየሱስ ቁስሌን ፈውሶ ያረገኝ ደህና አከብረዋለው ክብሬ ነውና (4x)