Song Lyrics

ውበት እና ግርማህ

Nahom Markos
Ewunetegna Selam
አዝ፦ ውበት እና ግርማህ ያማረ ሞገስህ እጅግ የከበረ ዝናህን ሰምቼ መጣሁ ከሰማሁት በላይ ሆኖ አየሁ አስገረመኝ አገዛዝህ ሁሉን በፍቅር ይዘህ አያልቅም ቢነገር ስራህ ጌታዬ እጅግ ልዩ ነህ ልዩ ነህ (3x) ጌታዬ እጅግ ልዩ ነህ (2x) ከአማልክት መካከል እንዳንተ ያለ ማነው በላይ በሰማይ በታች በምድር አንተን የሚመስል አጣሁ ኃያልና የተፈራህ ሥልጣናት ሁሉ በእጅህ ነው መንግሥትህ ዘለዓለም እጅግ የጸና ነው ዝናህን አውርቼ አልጨርሰው አይበቁኝምና ቃላት ለመግለጽ የአንተን ማንነት ስለዚህ ዝም ብዬ ላምልክ ሕይወቴን ለአንተ ላስገዛልህ (2x) አዝ፦ ውበት እና ግርማህ ያማረ ሞገስህ እጅግ የከበረ ዝናህን ሰምቼ መጣሁ ከሰማሁት በላይ ሆኖ አየሁ አስገረመኝ አገዛዝህ ሁሉን በፍቅር ይዘህ አያልቅም ቢነገር ስራህ ጌታዬ እጅግ ልዩ ነህ ልዩ ነህ (3x) ጌታዬ እጅግ ልዩ ነህ (2x) ብዙ ኃያላን የነበሩ ታላዝ ነን ብለው የተነሱ ዛሬ ቢፈለጉ አንዳቸውም የሉ ሞት አሸንፏቸው ተረሱ አንተ ግን ያለህ የነበርህ ለዘለዓለም ትኖራለህ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ የሚስተካከልህ የሌለህ ስለ አንተ ዘምሬ መቼ/መች ጠገብኩ (2x) ሥምህን ጠርቼ አልረካሁ (2x) ያንስብሃል ኢሄ አይበቃህ (2x) ከዚም በላይ ክብር ይብዛልህ (2x) አይበቃህምና ልጨምር ገና ከልቤ ይፍለቅ ብዙ ምሥጋና (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection