Song Lyrics

አባትነትህ

Abatneth

Frehiwot Abebaw
Yemeskelu kal
ትልቁ እግዚአብሔር ለኔ ለትንሿ አባት ነው ዘመድ ኩራት መጏደጃ ልክ እንደ አንድ ልጅ እንደ ብቸኛ የምትሳሳልኝ የነፍሴ እረኛ ትርፍ አይደለሁም ለቤትህ ወይ በጎደለ ልሞላ ብጠፋ ፈላጊዬ እትተካኝም በሌላ ዘጠና ዘጠኝ እያሉህ ሞልቶ እያለ በመንጋ አይኖችህ ክርትት እያሉ እኔን አንዲቷን ፍለጋ ባጠፋም ልጅህ ነኝ ባለማ በመልካም በክፉ ብታማ ውድ ነው የእኔ ልጅነት በደል ያልፋል አባትነትህ ነፍሴን መለስካት ስለ ስምህ በፅድቅ መራኸኝ ስለ ስምህ ቀንና ለሊት ስለ ስምህ ተከታተልከኝ ስለ ስምህ ልክ እንደ አንድ ልጅ እንደ ብቸኛ የምትሳሳልኝ የነፍሴ እረኛ አባ አባቴ እያልኩኝ ወደ ዙፋንህ ስጠጋ ከብዙ ጥፋት በኋላም አልተለወጠም ፀጋህ ቀድሞስ መቼ ተወደድኩኝ በጨዋነቴ በእኔ ስራ አንተው ዘንድ አይደለም ወይ የፍቅርህ መነሻ ስፍራ ባጠፋም ልጅህ ነኝ ባለማ በመልካም በክፉ ብታማ ውድ ነው የእኔ ልጅነት በደል ያልፋል አባትነትህ ላንተ የዋለ ሳይታጣ እኔን ቁምነገር እድርገህ መጣ ባልበቃም እንኳን ባልመችህ እየታገስከኝ አለሁ ቤትህ ልክ እንደ አንድ ልጅ እንደ ብቸኛ የምትሳሳልኝ የነፍሴ እረኛ በመኖሬ ደስ የሚልህ በመጥፋቴ የሚያምህ አባቴ ነህ ከአባትም አባት እድሜ ዘመኔን የምኮራበት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection